lower omo valley

በዓለም ቅርስነት የተመዘገበው የታችኛው ኦሞ ሸለቆ የጎብኚዎች እንቅስቃሴ የሰመረ እንዲሆን የትበብር ሥራን ለማጠናከር ምክክር ተደረገ፤

 

በዓለም ቅርስነት የተመዘገበው የታችኛው ኦሞ ሸለቆ እና በአካባቢው የሚገኙ ድንቅ የባህል እሴትን በቱሪዝም ሀብትነት የመጠቀም አቅም ለማሳደግ ምክክር ተደርጓል። የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ስለሺ ግርማ እና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ወይኒቱ መልኩ በአዲስ መልክ ከተዋቀረው የኢትዮጵያ አስጎብኚ ድርጅቶች ማህበር (ETOA) ቦርድ አባላት ጋር ሰፊ ውይይት አድርገዋል። በውይይቱም በደቡብ ኢትዮጵያ የጉብኝት ማዕከሎችን የማስፋፋት፣ የቱሪስትና-ደህንነት፣ የጉብኝት ክፍያ ስርዓት እንዲሁም አካባቢውን በዘላቂነት ይበልጥ የማልማትና የማስተዋወቅ ሥራዎች በቅንጅት ለማከናወን በሚያስችሉ የአሠራር ሂደቶች ዙሪያ ውይይቱ ተከናውኗል።

 

‎የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቱሪዝም ቢሮ ማህበራዊ ሚዲያ ገጾችን ይወዳጁ፣

 
 
 
 
 
 

Leave a Comment

Prove your humanity: 2   +   5   =