ato teferi

“የቱሪዝም ዘርፉን በዲጂታል በማዘመን በተመጠነ የሰው ሃይልና ሀብት መምራት ይገባል”: – አቶ ተፈሪ አባተ

በምክትል ርዕሰ መስተደድር ማዕረግ የሶዶ ክላስተር አስተባባሪና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈሪ አባተ በተገኙበት የክልሉ ቱሪዝም ቢሮ የ2019 ዓ.ም የበጀት ዕቅድ ተገምግሟል።
የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ በክልል ተቋማት የ2019 ዓ.ም የበጀት ዕቅድ ዝግጅት ላይ የ”በጀት ሰሚ” ፕሮግራም መድረክ እያካሄደ መሆኑ ይታወቃል።
በመድረኩም የቢሮው የ2018 በጀት ዓመት የበጀት አፈጻጸም ሪፖርት የተገመገመ ሲሆን፣ በቀጣዩ በጀት ዓመት እንዲተገበሩ የታቀዱ የፊዚካል እና የፋይናንሺያል ሥራዎች መሪ ዕቅድ ቀርቦ ሰፊ ምክክር ተደርጎበታል።
አቶ ተፈሪ በዚሁ ወቅት፥ ክልሉ የበርካታ ተፈጥሯዊና ባህላዊ መስህቦች የሚገኝበት መሆኑን ጠቅሰው፥ ቅርሶችን በመጠበቅና በመንከባከብ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ማሳደግ ይገባል ብለዋል።
የቱሪዝም ዘርፉን በዲጂታል በማዘመን በተመጠነ የሰው ሃይልና ሃብት ሊመራ እንደሚገባም አሳስበዋል።
የበጀት ሰሚ ፕሮግራም በክልል ደረጃ የሀብት አጠቃቀም ውጤታማነትን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሣሪያ መሆኑ ተገልጿል።
አሠራሩ በመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር ውስጥ ግልጽነትን፣ ተጠያቂነትን እና ፍትሐዊ የበጀት ክፍፍልን ለማስፈን የጎላ ሚና እንደሚጫወት ተጠቁሟል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቱሪዝም ቢሮ ማህበራዊ ሚዲያ ገጾችን ይወዳጁ፣
‎‎ቴሌግራም፦‎https://t.me/southethiotourismbureau
‎‎ዋትስአፕ፦‎https://whatsapp.com/channel/0029Vb7ImLwHgZWliFb0Tm2k Follow, Subscribe, like, Comment and Share በማድረግ ቤተሰብ በመሆን ይወዳጁ።

Leave a Comment

Prove your humanity: 9   +   7   =